Totot Traditional restaurant is an Ethiopian restaurant in Addis Ababa, with cultural dishes, mainly known for our “Kitfo”, Traditional Ethiopian dish and a beautifully designed interior as well as exterior. We offer a great dining experience and a show with our band and traditional dancers. Tourists and local customers have enjoyed the eminence of Ethiopian cuisine and customary framework of our restaurant for the past nine years. We strive to make your stay as wonderful as possible.
ይህ የኢትዮጰያዊነት ድንቅ አሻራ የታተመበት የአንድ ባህላዊ ምግብ አዳራሽ አጭር ታሪክ ነው ። ቶቶት የባህል አዳራሽ ይባላል መጠሪያው ። ቶቶት ስርዎ ቃሉ ከጉራጊኛ ቋንቋ የተመዘዘ ነው። ትርጉሙም በስራ ፣ በትጋት እናድጋለን ፣ ከፍ እንላለን ማለት ነው ። በ2001 ዓመተ ምህረት የተመሰረተው ቶቶት ዛሬም እንደ ዝግባ እየረዘመ እንደ ዋርካ እየሰፋ ጉዞውን ቀጥሏል ። ቶቶት ብዙ ነው ፣ የጣፋጭ ምግቦች ማዕከል፣ የቅርስ እና የማንነት አሻራዎች መደብር ፣ የስብዕና እና የስነ ልቦና ማደሻ እና ማበልጸጊያ ፣ የኪነ ጥበብ እና የስነ ጥበብ አውዳማ ነው ቶቶት ።